ENAB TECH PODCAST

ENAB TECH PODCAST

በዚህ ፖድካስት በሳምንቱ የነበሩ በተለይ አይነስውራንን የሚመለከቱ ዜናዎች፣ ለቴክኖሎጂ ጀማሪዎች ተደራሽ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣ በቴክኖሎጂ ልምድ ላላቸውም ቢሆን የሚሆኑ አዳዲስ አፕሊኬሽኖች እና አገልግሎቶችን ማቅረብ እና ከአድማጮች ለሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመስጠት ማብራሪያ ገለጻ የሚደረግበት ሳምንታዊ ፖድካስት ነው።

Episodes

August 24, 2024 29 mins

በዝግጅቱ ቀዳሚ ክፍል የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ከስክሪናችሁ ኬብል የሚወጣን ጨረር በመመልከት ብቻ ስክሪን ላይ ያለውን ጽሁፍ መለየት ስለመቻሉ፤ እንዲሁም ጉግል ሰርች ህገወጥ ሞኖፖሊ ነው ተብሎ የተፈረደበት ስለመሆኑ የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ መጨረሻ ክፍል፣ በቴሌብር ገንዘብ ማስተላለፍን ጨምሮ አንዳንድ ጉዳዮችን እንዴት እንደምንፈጽም በተግባር እንቃኛለን። ከአድማጮች ጥያቄዎች ውስጥ፥- የኮምፒውተር ቁልፍ አቀማመጡ ከተለመደው ተዘበራርቆ አስቸገረኝ። ምሳሌ፣ ዜድ ወደ ደብልዩ፣ ደብልዩ ወደ ዜድ እየተቀያየሩ፣ እንዴት ባደርገው ይስተካከላል? የምጠቀመው የጥር 20 ጂሺዎ ቨርዥን ነው። እና በሳምሰንግ ጀይ 2 ፕሮ ማይ ፋይልስ ውስጥ የተወ...

Mark as Played

ጤና ይስጥልን፣ እንዴት አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በኤፒሶዱ የመጀመሪያ ክፍል በሆነው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት ስካይፕ በተባለው የቪዲዮ መደዋወያ አፕሊኬሽኑ ማስታወቂያዎችን ማሳየት ሊያቆም ስለመሆኑ እና ጉግል በክሮም ብራውዘሩ ሴቭ የተደረጉ ፓስወርዶችን በአፕዴት ችግር ምክንያት ለ18 ተከታታይ ሰአታት ማሳየት ሳይችል መቅረቱን የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ቀጣይ በሆነ የዝግጅት ክፍል፣ ቴሌብር አፕሊኬሽንን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት እንደምንከፍት አጠቃቀሙን በተግባር እየሞከርን እናስተዋውቃችኋለን። ቴሌብር በጣም በርካታ ክፍሎች ስላሉት በተለየ እንድናተኩርበት የምትፈልጉት የቴሌብር ክፍል ካለ ይህ ዝግጅት ከተለቀቀበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 8 ሰ...

Mark as Played

ሰላም፣ እንዴት አላችሁ? የኢናብ ቴክ ፖድካስት ተከታታዮች፤ በዚህ ክፍል የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ኤንቪዲኤ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና ማይክሮሶፍት በዊንዶውስ 11 ዋን ድራይቭ የተባለው አገልግሎቱን በሙሉ ስክሪን ማስታወቂያ ለተጠቃሚዎቹ በማድረስ ማስቸገሩን የሚሉትን መረጃዎች እናወራችኋለን። ዛሬ በሚጀምረው የሞባይል ወርልድ የዝግጅት ክፍል፣ ሁላችንም በተለያየ አጋጣሚ ስለምንሰማው እና በርካቶቻችን በተለያየ መጠን እየተጠቀምነው እንደሆነ ስለምንገምተው ቴሌብር አገልግሎት እናስተዋውቃችኋለን። በተለየ እንድናተኩርበት የምትፈልጉት የቴሌብር ክፍል ካለ አስተያየት እና ጥቆማዎችን ላኩልን። ከአድማጮች ጥያቄዎች መካከል፥- ኤይር ድሮፕ ከተባሉት ውስጥ ለስክሪን ሪደር...

Mark as Played

እንዴት ናችሁ? የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ ዛሬ ደግሞ ይዘነው በመጣነው ኤፒሶድ፣ በቀዳሚው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ጉግል ኩኪስ የተባሉት ቴክኖሎጂ ለማስቀረት ያወጣውን እቅድ ስለመቀልበሱ እና ክራውድ ስትራይክ ድርጅት ፋልኮን የተባለው አንቲቫይረሱ አፕዴት ሲያደርግ በአለማቀፍ ደረጃ ያስከተለው ቀውስ እንዳይደገም ስለሚያደርገው ጥረት የሚመለከቱ መረጃዎችን እናጋራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን አጠቃቀም የመጨረሻ ክፍል፣ በስልካችን አፕሊኬሽኑን እንዴት እንደምንቆጣጠር እና ካሻንም በስልካችን ፒሲ ላይ ያለውን ሙዚቃ እንዴት እንደሚያሰማን እንመለከታለን። አድማጮች ከላኳቸው ጥያቄዎች ውስጥ፥- የአንድሮይድ ቨርዥን ከአምራቹ ፍቃድ ውጪ አፕዴት ስ...

Mark as Played

ሰላም ሰላም የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፣ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር የሆነው ጂሺዎ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ስላካተታቸው አዳዲስ ነገሮች እና ያደረጋቸውን ማሻሻያዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ እያስተዋወቅነው ባለው ዋን ባይ ዋን በተባለው የኦዲዮ ማጫወቻ አፕሊኬሽን ቀሪ ሴቲንጎችን እንዴት እንደምናስተካክል፣ ድምጽን እንዴት አፍጥነን እንደምናጫውት፣ ያለንበትን የትራክ ቦታ እንዴት መዝግበን ማስቀመጥ እንችላለን? "በተለይ ለኦዲዮ መጻህፍት ይሄ ጠቃሚ ነው፤" ያሉንን ትራኮች በቅምሻ እየቆነጠረ እንዲያሰማን እንዴት እናደርጋለን የሚሉትን አጠቃቀሞች እንቃኛለን። ከአድማጮች ለተነሱ በጂሺዎ ስክሪን ሪደር ኮንታክቶቼን በሙሉ ሊያነብልኝ አል...

Mark as Played

እንዴት ቆያችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች? በቅድሚያ በሚቀርበው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች የዝግጅቱ ክፍል፣ በክራውድ ስትራይክ የአንቲቫይረስ ድርጅት አፕዴት ያስከተለው ቀውስ በመጠኑም ቢሆን መቀጠሉን፣ ሳምሰንግ በስልኮቹ አንድሮይድ ያጋጠመን የደህንነት ክፍተት ባልተለመደ ፍጥነት ፈፕዴት ሊለቅ ስለመሆኑ እንዲሁም ጉግል ክሮም ፋይል ዳውንሎድ ስታደርጉ ለምንድን ነው የምታወርዱት ብሎ መጠየቅ መጀመሩን የሚሉትን መረጃዎች እንቃኛለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስለዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን አጠቃቀም የምናሳይበት ቀጣይ ክፍል ከሴቲንጎች ውስት ስለስፔሻል ሴቲንግ እና ስለዊንዶውስ ሴቲንግ የተመለከተ ዝግጅት ይዘናል። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል የምር!...

Mark as Played

ጤና እና ሰላም ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት ተከታታዮች። ኤፒሶዱን በምናስጀምርበት የቴክኖሎጂ መረጃዎች፣ የአንቲቫይረስ አፕዴት በፈጠረው የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት በመላው አለም የሚገኙ ትላልቅ ኩባንያዎች እና ተቋማት አገልግሎቶቻቸው ተቋርጠው ስለመዋላቸው፣ ዊንዶውስ አዲስ የአፕዴት መንገድ ስለማስጀመሩ እና የአፕል አይኦኤስ ኦፐሬቲንግ ሲስተም በቀላሉ ሀክ ማድረግ አለመቻሉን ይህንን የሚሰራ ተቋም ስለማስታወቁ የሚሉትን መረጃዎች እንነግራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ስለዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን አጠቃቀም የምናሳይበት ቀጣይ ክፍል ሴቲንጎችን ስለማስተካከል እንመለከታለን። ከአድማጮች ለተነሳ አስተያየትም ምላሽ አካትቻለሁ። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://...

Mark as Played

ሰላም እንዴት አደራችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች። በዛሬው ኤፒሶድ ቀድሞ በሚቀርበው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 ይዞት ሊመጣ ነው ስለተባለው ስልካችንን እንደኮምፒውተር መጠቀም የሚያስችለን አገልግሎት እና ማይክሮሶፍት ወደ ፍልስጥኤም የሚደውሉ ደንበኞቹን አካውንት እየሰረዘ መሆኑን ስለመዘገቡ የሚሉ መረጃዎችን እንቃኛለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ማስተዋወቅ በጀመርነው የዋን ባይ ዋን አፕሊኬሽን ፕለጊኖችን እንዴት እንደምናካትትበት እና የኦዲዮ ሴቲንጎችን በከፊል እንፈትሻለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም፣ አበቃለት ብዬው የነበረውን የማይክሮሶፍት ኤክሴል፣ ጠቃሚ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ መጨመር አለባቸው ብዬ ካሰብኳቸው ፎርሙላዎች የመጀመሪያውን ደረጃ መስጠትን የሚ...

Mark as Played

እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት የመጨረሻ ኤፒሶድ ይዘን መጥተናል፣ ብያችሁ እንደነበር ይታወሳል። ለፈጠርኩት የመረጃ ክፍተት ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ፖድካስቱ የሚቀጥል መሆኑን የተነገረኝ ስለሆነ እነሆ ቀጣይ ክፍል ይዤ መጥቻለሁ። ዝርዝሩን ከኤፒሶዱ ታገኙታላችሁ። እንደተለመደው፣ በቀዳሚው የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ክፍል፣ ጃውስ ባደረገው ማሻሻያ ስለጨመራቸው ነገሮች እና ጃፓን ፍሎፒ የተባለው እጅግ የቆየ ቴክኖሎጂ ከመንግስት አገልግሎቶች ማስወገድ ስለመቻሏ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ፣ ዋን ባይ ዋን ስለሚባል የኦዲዮ ምቹ ማጫወቻ አስተዋውቃችኋለሁ። ከአድማጮች ለተነሳ ጥያቄዎችም ምላሾችን አካትቻለሁ። ፖድካ...

Mark as Played

እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት የመጨረሻ ኤፒሶድ ይዘን መጥተናል። በዚ በመጨረሻ ክፍል ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ኤንቪዲኤ በቨርዥን 2024.2 ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች እና አፖል ኩባንያ በአይኦኤስ የወደፊት ኦፐርቲንግ ሲስተሙ ቨርዥን 18 ከተደራሽነት ጋር ስላካተታቸው ነገሮች መረጃዎችን እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የመጨረሻ ክፍል ከስልካችን በቀትታ ፕሪንት እያደረግን በተግባር እንሞክራለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ክፍል ስለፎርሙላዎች እና ስለፋንክሽንስ እንዴት እንደምንጠቀም እናያለን። ከአድማጮች ለተነሳ ጥያቄዎችም ምላሾችን አካተናል። ፖድ...

Mark as Played

ሰላም፣ ጤና ይስጥልን፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ዩቲውብ በስልካቸውም ሆነ በኮምፒውተራቸው ላይ አድ ብሎከሮችን ጭነው ዩቲውብን ለመጠቀም የሚሞክሩ ተጠቃሚዎቹን ቪዲዮዎችን መመልከት እንዳይችሉ አልያም የሚመለከቱትን ነገር እንዳይመች የማድረግ ሙከራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል የሚለውን መረጃ እናጋራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የምናቀርበው ቀጣይ ክፍል ሞቢሊቲ ፕሪንትን በስልካችን ላይ እንዴት እንደምናስተካክለው በተግባር እየሞከርን እንመለከታለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ቀጣይ ክፍሉ፣ የከፈትነውን ባዶ የስፕሬድ ሺት ዶኪውመንት ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት ሴቭ እንደምናደር...

Mark as Played

እንደምን አላችሁ? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ይህ እኔ የማቀርበው ዝግጅትም ሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች ፖድካስት እየተባለ ሲጠራ ሰምታችኋል። በዚህ ዝግጅት ስለ ፖድካስት ምንነት እና ፖድካስትን ለመከታተል እና ለማድመጥ ከሚረዱን የስልክ አፕሊኬሽኖች አንዱ ስለሆነው ፖኬት ካስት የሚስተካከልበትን መንገድ እና አጠቃቀም እናብራራለን። ሙሉ ዝግጅቱን አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት ማድመጫ አፕሊኬሽኖች https://pnc.st/s/enab-tech-podcast የሚለውን ሰብስክራይብ በማድረግ አድምጡ። ጥያቄ፣ አስተያየታችሁን 0973034577 ላይ የጽሁፍ፣ ደውላችሁ የድምጽ መልእክት በማስቀመጥ ወይም ...

Mark as Played

ሰላም የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ከዚህ በፊት በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች ዘገባዬ የነገርኳችሁ አንድሮይድ 15 ቤታ ወይም የሙከራ ቨርዥን አካል ሆኖ ይለቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው ቶክ ባክ 15.0 ስላካተታቸው ነገሮች መረጃ ይዘናል። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የምናቀርበው ቀጣይ ክፍል በሁሉም አይነት ፕሪንተሮች ከስልካችን ፕሪንት ለማድረግ ስለሚያስችለን ሞቢሊቲ ፕሪንት አጫጫን እና ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሰራ ሴቲንጎቹን እንዴት እንደምናስተካክል የሚያሳይ ዝግጅት አቅርበንላችኋል። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ቀጣይ ክፍሉ፣ በማይክሮሶፍት ኤክሴል ሴቲንጎቹን እና የዶኪውመንት አማራጮችን የምናገ...

Mark as Played

እንዴት ናችሁ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አፕል ኩባንያ በኮምፒውተር እና በስልክ መካከል ደረጃ ላይ የሚገኙትን አይፓድ የተባሉትን የመጨረሻውን ቴክኖሎጂ ያካተቱ ታብሌቶቹን ለገበያ ማቅረቡን፣ ማይክሮሶፍት ወርድ ከተለያዩ ቦታዎች በኮፒ ፔስት ጽሁፍ ስታደራጁ ያጋጥም የነበረውን የቅርጽ መዘበራረቅ የሚያስቀር አፕዴት ስለመልቀቁ እንዲሁም ኦፕን ኤአይ የተባለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሰሪ ድርጅት ቻት ጂፒቲ በተባለው አገልግሎቱ ከሰው ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ የሆነ አዲስ ማሻሻያ ለህዝብ በይፋ ስለማቅረቡ የሚሉትን መረጃዎች በዝርዝር እንመለከታለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልካችን ፕሪንት ስለማድረግ የምናቀርበው ቀጣይ ክፍል በሁሉም አይነት ፕሪንተ...

Mark as Played

ሰላም ጤና ይስጥልን፣ እንደምን አላችሁ፤ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ አንድሮይድ 15 በ2ኛ ሙከራ ቨርዥኑ አዲስ ስላካተታቸው ነገሮች እንዲሁም ታዋቂው እና ተወዳጁ የሞባይል ቪዲዮ ማጋሪያ እና መመልከቻ ቲክቶክ አፕሊኬሽን በአሜሪካ ሀገር ስላጋጠመው ተግዳሮት ዝርዝር እናወራችኋለን። በሞባይል ወርልድ ዝግጅት፣ በስልኮቻችን ፕሪንት ስለማድረግ ማብራሪያ እናቀርባለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ቀጣይ ክፍሉ በማይክሮሶፍት ኤክሴል ዶኪውመንት ውስጥ ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ የሚረዱ ተጨማሪ መንገዶችን እንቃኛለን። ከአድማጭ ለተነሱ ጥያቄ እና አስተያየቶች ማብራሪያም አካተናል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም ...

Mark as Played

ሰላም ሰላም፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ዋነኛ ስክሪን ሪደር የሆነው ጃውስ ፎር ዊንዶውስ በሜይ 2024 አፕዴት በሚል አዲስ በለቀቀው ማሻሻያ ስላደረጋቸው ለውጦች እና ማስተካከያዎች እንዲሁም ሳም ኦልትማን የተባለው የቴክኖሎጂ ባለሀብት የድሆችን የግል መረጃ ለመግዛት ሀምሳ ዶላር እየከፈለ ስለመሆኑ የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን።
በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት የመጨረሻ ክፍል፣ በማይክሮሶፍት ወርድ እንዴት በተግባር ፕሪንት እንደምናደርግ እየሞከርን እንተዋወቃለን። በመሰረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም ዝግጅት፣ ስለማይክሮሶፍት ኤክሴል በሚያብራራው ቀጣይ ክፍሉ በማይክሮሶፍት ኤክሴል ዶኪውመንት ው...

Mark as Played

ሰላም? የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ ኮምፒውተርን ስንጠቀም ለትምህርትም ሆነ ለስራ መሰረታዊ ከሆኑ አፕሊኬሽኖች ውስጥ ዋነኛው የማይክሮሶፍት ኦፊስ ጥቅል ነው። ከዚህ ጥቅል ውስጥ ደግሞ መሰረታዊ ከሆኑት ውስጥ አንደኛ ሊባል የሚችለው ማይክሮሶፍት ወርድ ነው። ለኮምፒውተርም ሆነ ለማይክሮሶፍት ወርድ በስክሪን ሪደር ለመጠቀም መጀመሪያቸው ለሆኑ መሰረታዊ የሆኑ አጠቃቀሞችን ያሳያል ብለን ያሰብነውን ሙሉ ቱቶሪያል አቅርበናል። ሙሉውን አውርዱ እና አድምጡት። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት ማድመጫ አፕሊኬሽኖች https://pnc.st/s/enab-tech-podcast የሚለውን ሰብስክራይብ በማድረግ አድምጡ። ጥያቄ፣ አስተያ...

Mark as Played

እንደምን አላችሁ ፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የአንድሮይድ ስክሪን ሪደር ጂሺዎ አዲስ በለቀቀው ቨርዥን ይዟቸው ስለመጣቸው ነገሮች ዝርዝሩን እናወራችኋለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ ፕሪንተራችንን መጠቀም ከመጀመራችን በፊት ስለሚደረገው ፕሪንተርን ከኮምፒውተር ጋር የማስተዋወቅ ሂደትን በተግባር እየሞከርን እንመለከታለን። ለአድማጮች ጥያቄ፣ የማይክሮሶፍት ኤክሴል የሚከፈትበትን ተጨማሪ መንገድ ከአድማጭ በተገኘ ግሩም ጥቆማ አማካይነት የምናብራራ ሲሆን ሌሎችንም ማብራሪያዎች ይዘናል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት ማ...

Mark as Played

ሰላም ጤና ይስጥልን፣ የኢናብ ቴክ ፖድካስት አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ ማይክሮሶፍት በስቶር ውስጥ የሚገኙ አፖችን በሌላ አማራጭ የሚጫኑበትን መንገድ ስለማመቻቸቱ፣ በአሜሪካ የሚገኙ የፖሊስ ተቋማት የጂፒኤስ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ሌቦችን በመኪና ማሯሯጥ ማቆማቸው ስለመዘገቡ እንዲሁም አፕል በአይፎን ስልኮቹ እና በሌሎቹ መሳሪያዎቹ ጋር በመያያዝ ሲጠፉ ለማግኘት የሚረዳ አገልግሎቱ የንጹሀን ግለሰቦች ቤት በፖሊስ ተሰብሮ እንዲገባ እና ንብረታቸው እንዲበለሻሽ ምክንያት መሆኑን የሚሉትን መረጃዎች እንመለከታለን። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ አንድ ፕሪንተር ያሉትን ክፍሎች በአካል እየዳበስን ማብራሪያ እናቀርባለን። ለአድማጮ...

Mark as Played

እንደምን አላችሁ፣ የኢናብ ቴክ አድማጮች፤ በቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች፣ የዊንዶውስ ስክሪን ሪደር የሆነው ኤንቪዲኤ በአዲስ ቨርዥኑ ይዟቸው ከመጣቸው ነገሮች ውስጥ በተለይ በዋና ዋና ጉዳዮች ዘርዘር ያለ ማብራሪያ አቅርበናል። በኮምፒውተር ቲፕስ ኤንድ ትሪክስ ዝግጅት፣ ስለፕሪንተር የምናስተዋውቅበት ዝግጅት ቀጥሎ፣ ስለፕሪንተር አይነቶች ምንነት እናቀርባለን። ከአድማጮች ከተነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች፣ ስለኮምፒውተር ፎርማት አደራረግ ዙሪያ፣ ስለኢትዮቴሌኮም ቴሌብር ኢንጌጅ እና ስለማይክሮሶፍት ኦፊስ 2010 አክቲቬተር ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያዎች አቅርበናል። ፖድካስቱን ለመከታተል፣ በቴሌግራም https://t.me/enabtechpod ሰብስክራይብ አድርጉ። በፖድካስት ማድመጫ አፕሊኬሽኖች...

Mark as Played

Popular Podcasts

    If you've ever wanted to know about champagne, satanism, the Stonewall Uprising, chaos theory, LSD, El Nino, true crime and Rosa Parks, then look no further. Josh and Chuck have you covered.

    My Favorite Murder with Karen Kilgariff and Georgia Hardstark

    My Favorite Murder is a true crime comedy podcast hosted by Karen Kilgariff and Georgia Hardstark. Each week, Karen and Georgia share compelling true crimes and hometown stories from friends and listeners. Since MFM launched in January of 2016, Karen and Georgia have shared their lifelong interest in true crime and have covered stories of infamous serial killers like the Night Stalker, mysterious cold cases, captivating cults, incredible survivor stories and important events from history like the Tulsa race massacre of 1921. My Favorite Murder is part of the Exactly Right podcast network that provides a platform for bold, creative voices to bring to life provocative, entertaining and relatable stories for audiences everywhere. The Exactly Right roster of podcasts covers a variety of topics including historic true crime, comedic interviews and news, science, pop culture and more. Podcasts on the network include Buried Bones with Kate Winkler Dawson and Paul Holes, That's Messed Up: An SVU Podcast, This Podcast Will Kill You, Bananas and more.

    The Joe Rogan Experience

    The official podcast of comedian Joe Rogan.

    The Breakfast Club

    The World's Most Dangerous Morning Show, The Breakfast Club, With DJ Envy, Jess Hilarious, And Charlamagne Tha God!

    New Heights with Jason & Travis Kelce

    Football’s funniest family duo — Jason Kelce of the Philadelphia Eagles and Travis Kelce of the Kansas City Chiefs — team up to provide next-level access to life in the league as it unfolds. The two brothers and Super Bowl champions drop weekly insights about the weekly slate of games and share their INSIDE perspectives on trending NFL news and sports headlines. They also endlessly rag on each other as brothers do, chat the latest in pop culture and welcome some very popular and well-known friends to chat with them. Check out new episodes every Wednesday. Follow New Heights on the Wondery App, YouTube or wherever you get your podcasts. You can listen to new episodes early and ad-free, and get exclusive content on Wondery+. Join Wondery+ in the Wondery App, Apple Podcasts or Spotify. And join our new membership for a unique fan experience by going to the New Heights YouTube channel now!

Advertise With Us
Music, radio and podcasts, all free. Listen online or download the iHeart App.

Connect

© 2025 iHeartMedia, Inc.